በኬንያ የሚኖሩ የቡርጂ ማህበረሰብ የዳያስፖራ አባላት በኤምባሲው በመገኘት እየተጠናቀቀ ያለውን የህዳሴ ግድብ የመጨረሻ ምዕራፍ የቦንድ ግዢ የፈፀሙ ሲሆን፣ በዓለቱ እያንዳንዱ ግለሰብ ከ100 እስከ 1000 (አንድ ሽህ) የአሜሪካ ዶላር ድረስ ቦንድ ገዝተዋል። በአጠቃላይ 8050 (ስምንት ሽህ ሀምሳ) የአሜሪካ ዶላር የቦንድ ግዢ ተካህዷል።
በኬንያ የሚኖሩ የቡርጂ ማህበረሰብ የዳያስፖራ አባላት በተለያዩ ጊዜያት በሚደረጉ አገራዊ ጥሪዎች ላይ በንቃት የሚሳተፉ ሲሆን፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት የመጨረሻ ምዕራፍ የቦንድ ግዢ ላይ በከፍተኛ ንቃት ስሳተፉ ቆይተዋል።
ክቡር አምባሳደር ጀኔራል ባጫ ደበሌ በኤምባሲው በመገኘት የቦንድ ግዢ ለፈፀሙ በኬንያ የቡርጂ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በራሳቸው እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ስም ምስጋናቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ላሳዩት ከፍተኛ የአገር ፍቅር እና ተነሳሽነት አድናቆታቸውን ገልፀውላቸዋል ።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
INSTAGRAM