በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከንቾ ሻቻ ጎዝዴ ቀበሌ ለደረሰ አደጋ ከ640 000 (ስድስት መቶ አርባ ሺህ) ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
(ሐምሌ 27 ቀን 2026 ዓ.ም ናይሮቢ፣ ኬንያ) በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከንቾ ሻቻ ጎዝዴ ቀበሌ የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በናይሮቢ የኢፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ እያስተባበረ በሚገኘው በዚህ ድጋፍ እስካሁን አምስት ሺ ሁለት መቶ አምሳ (5250) ዶላራ፣ አንድ መቶ አስር ሺ (110,000) የኬንያ ሽልንግ እንዲሁም አስር ሺ ብር በአጠቃላይ ከ640 000 (ስድስት መቶ አርባ ሺህ) ብር በላይ ተሰብስቧል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ናይሮቢ ሚሲዮን ዲፕሎማቶች እና አጠቃላይ ሰራተኞች በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አስከፊ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎቻችን የወገን አለኝታነታቸውን ለመግለፅ በክቡር የሚሲዮን መሪ አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ አነሳሽነት የአንድ ወር ደሞዛቸውን በመለገስ በአጠቃላይ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት (247,345) የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡ የሚታወስ ነው ።
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከንቾ ሻቻ ጎዝዴ ቀበሌ በደረሰው አደጋ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን ማጣታቸው እና በርካቶች ከቤት ንብሬታቸው መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከታች በተዘረዘሩ የባንክ አድራሻዎች ድጋፍ ማድረግ የሚትችሉ መሆኑን በአክብሮት መግለፅ እንወዳለን።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
INSTAGRAM